All insights & news
licensing 7 Apr 2024

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ፍትሕ ሚኒስቴር በሀገራችን ታሪክ የመጀመሪያ የሆነዉን የጥብቅና ድርጅት (Law Firm) ፈቃድ ሰጠ

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ፍትሕ ሚኒስቴር በሀገራችን ታሪክ የመጀመሪያ የሆነዉን የጥብቅና ድርጅት (Law Firm) ፈቃድ ሰጠ

የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. መንግስት የሕግ አገልግሎት ዘርፍን ለማሻሻል የተለያዩ እርምጃዎችን እየወሰደ ሲሆን ከእነዚህም መካከል አዲስ የፌዴራል ጥብቅና አገልግሎት ፍቃድ አሰጣጥ እና አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 1249/2013 ማዉጧቱ የታወሳል። ከዚሁ ጋር በተያያዘ በቅርቡ የኢትዮጵያ የፌዴራል ጠበቆች ማህበር መመስረቱና አመራሮች ተመርጠዉ ሥራ መጀመራቸዉ ይታወቃል።

የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ፍትሕ ሚኒስቴር ከአዲሱ የኢትዮጵያ የፌዴራል ጠበቆች ማህበር እና ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር አዋጁን ተግባራዊ ለማድረግ ዝርዝር የአሰራር መመሪያዎችና ዉስጠ ደንብ መቅረጽን ጨምሮ ወደ ሥራ ገብቷል። በአዲሱ የጠበቆች አዋጅ አንቀጽ 37 መሰረት የፀና የጥብቅና ፈቃድ ያላቸው ቢያንስ ሁለት ጠበቆች አንድ ላይ በመሆን የጥብቅና ድርጅት ማቋቋም እንደሚችሉ ተደንግጓል።

በዚህም መሰረት የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ፍትሕ ሚኒስቴር የጥብቅና ድርጅቶች ፈቃድ መስጠት የጀመረ ሲሆን የመጀመሪያዉን ፈቃድ ሰጥቷል። በሚኒስቴር ዴኤታ ክቡር አቶ ዓለምአንተ አግደዉ ፈቃዱን በሰጡበት ወቅት፣ ለዜጎች የተሻለ ጥራት ያለዉ የሕግ አገልግሎት ለመስጠት ፈቃዱ ከፍተኛ ጠቀሜታ ያለዉ ነው ብለዋል።

ለፈቃድ ማመልከቻ የሚያስፈልጉ ሰነዶች: 1. ማህበሩን ለመመስረት በተስማሙ አባላት የተፈረመ ማመልከቻ 2. ከማመልከቻው ጋር በሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት የተረጋገጠ የመመስረቻ ጽሁፍ 3. በአባላት የተፈረመ ቃለ ጉባዔ 4. የሸሪኮች የሽርክና ስምምነት 5. አመልካቾች ጠበቆች መሆናቸዉ እና የታደሰ ፈቃድ ያላቸው መሆናቸውን የሚገልጽ ፈቃድ ኮፒ 6. ማህበሩ የመድህን ዋስትና ስለመግባቱ የሚያረጋግጥ ሰነድ

ማስታወሻ: ማመልከቻው ባምቢስ በሚገኘው የፍትሕ ሚኒስቴር ዋና መስሪያ ቤት ህንጻ 2ኛ ፎቅ ለጠበቆች ፍቃድ አስተዳደርና ነጻ የህግ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ይቀርባል።

Have a legal question?

Ready to Discuss Your Case?

Our advocates are ready to turn insight into action. Reach out for a confidential consultation.

Confidential & privileged Response within 24 hoursEthiopia's first law firm