
በአዋጅ ቁጥር 1243/2013 አንቀጽ 588(2) ላይ እንደተመለከተው ለጥንቃቄ ዕዳን መልሶ የማዋቀር ሥነ ሥርዓት የሚከፈተበት ሌሎች የሚመለከታቸው ገንዘብ ጠያቂዎች በሙሉ ድምጽ የሚፈቅዱ ከሆነ፤ በባለዕዳው ላይ እንደአሁን ባለ ወቅት የገጠመውን የፋይናንስ ችግር በተከሰቱ ያልታሰቡ ኹነቶች ምክንያት ተስፋ የሚጣልባቸው ተበዳሪዎች ውልን መሰረት ባደረገ መልኩ በጊዜ ዕዳቸውን ቀልጣፋ እና ውጤታማ በሆነ መልኩ መልሰው እንዲያዋቅሩ እና ሥራቸውን እንዲቀጥሉ ወይም የንግድ ሥራ እንቅስቃሴው በመንቀሳቀስ ላይ እንዳለ የንግድ ሥራ ለመሸጥ መዘጋጀት እንዲችሉ በማድረግ አሁናዊ የኢኮኖሚ ሁኔታቸውን ረተው እንዲወጡ ማስቻል ነው።
1. የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት
1.1. ክፍያ
ለሚሾሙት ለጥንቃቄ እዳን የማዋቀር ዘርፍ ባለሞያዎች ክፍያ በባለዕዳዋ/ው እና በዘርፉ ባለሞያዎች መካከል በሚደረግ ንግግር የሚወሰን ሲሆን ዋጋው መጠን በፍርድ ቤት መጽደቅ አለበት።
1.2. በጊዜ ረገድ
በአንቀጽ 618 መሰረት የሥነ ሥርዓቱ የቆይታ ጊዜ - ለጥንቃቄ ዕዳን መልሶ የማዋቀር ዕቅዱ ከሚመለከታቸው ገንዘብ ጠያቂዎች ጋር በአራት ወራት ውስጥ መጠናቀቅ ይኖርበታል። ተጨማሪ ጊዜ ሊሰጥ እንደሚችልም ሆኖ ይህ ጊዜ ከ8 ወር ሊበልጥ አይችልም።
2. የሥነ ስርዓቱ ተጠቃሚ / ባለዕዳ
ዕዳን መልሶ የማዋቀር ዕቅድ ማዘጋጀት፣ ከጥንቃቄ እዳን ማዋቀር ባለሞያዎችን ድጋፍ መጠየቅ እና ማግኘት (አንቀጽ 627)፣ የንግድ ስራውን በይዞታ ስራ አድርጎ መምራት፣ አስቀድመው ነጠላ እገዳ ከተላለፈባቸው ዕዳዎች በስተቀር ባለዕዳው በመደበኛ የሥራ ሂደት ውስጥ የሚከሰቱ ዕዳዎችን መክፈል ይኖርበታል። መደበኛ እዳ ክፍያ ማቋረጥ ለእንደገና ማደራጀት ወይም ኪሳራ ስርዓት ይዳርጋል። (ን.ሕ.ቁ 626 እና 702)
3. ለጥንቃቄ እዳን የማዋቀር ዘርፍ ባለሞያ/ዎች/
3.1. ግዴታዎች
ለጥንቃቄ ዕዳን መልሶ የማዋቀር ዘርፍ ባለሞያው ራሱን ችሎ: ሀ) ሥነ ሥርዓቱ ውስጥ የሚሳተፉትን ገንዘብ ጠያቂዎች መወሰን፣ ለ) ዕቅድ በማርቀቅ እና በመደራደር ባለዕዳውን ማገዝ፣ ሐ) የገንዘብ ጠያቂዎቹን ስብሰባዎች ጥሪ ማድረግና መምራት፣ መ) የባለዕዳውን እንቅስቃሴ መቆጣጠርና ሪፖርት ማቅረብ፣ ሠ) ዕቅዱን ለፍርድ ቤቱ ማስጸደቅ፣ ረ) ድርጅቱ ሲሸጥ ማዘጋጀት።
3.2. ሥልጣን
የባለዕዳዋ/ውን መሰረታዊ ንብረቶች ሽያጭ ማጽደቅ፤ ተጨማሪ የገንዘብ/ሒሳብ መረጃ እንዲቀርቡ ትዕዛዝ መስጠት፤ ገለልተኛ ባለሞያዎችን ሾሞ ኦዲት ማሰራት።
4. ባለገንዘብ/ቦች/
አንቀጽ 597 - ዋና መርህ: የገንዘብ ጠያቂዎችን ትክክለኛ ጥቅም ማስጠበቅ። መልሶ የማዋቀር ዕቅዱ በሁሉም ሚመለከታቸው ገንዘብ ጠያቂዎች ሙሉ ድምጽ መጽደቅ አለበት። ዕቅዱን ለማሻሻል ጥያቄ እና የአጸፋ-ሀሳብ የማቅረብ መብት አላቸው፤ ስብሰባ ላይ አስተያየት የማቅረብ እና የመሰማት መብት አላቸው።
5. ለጥንቃቄ ዕዳን መልሶ የማዋቀር ዕቅድ
ዕቅዱ በባለዕዳዋ/ው ተዘጋጅቶ፣ ባለሞያዎች ዝግጅቱን ይደግፋሉ። ተሳታፊ ባለገንዘቦች ሃሳብ የማቅረብ፣ የተቃውሞ እና የድጋፍ ድምጽ የመስጠት መብት አላቸው። ሂደቱ ከ4 ወራት መጠናቀቅ አለበት (ከ8 ወር አይበልጥም)። ዕቅዱ ሁሉም ተሳታፊ ባለገንዘቦች ሙሉ ድምጽ ማግኘት አለበት።
6. በዕቅዱ ሊካተቱ የሚችሉ
ሀ) የክፍያ ጥያቄዎች እንደገና የጊዜ ሰንጠረዥ ማውጣት (rescheduling)፣ ለ) የክፍያ ጥያቄዎችን መተው (waiver)፣ ሐ) የገንዘብ ዕዳ ሰነዶችን ማውጣት፣ መ) የክፍያ ጥያቄዎች ወደ አክሲዮን መቀየር፣ ሠ) ካፒታል መጠን መቀነስ ወይም መጨመር፣ ሸ) ነባር አክሲዮኖችን መሸጥ ወይም አዲስ ማውጣት፣ ቀ) አዲስ የፋይናንስ ምንጭ ማግኘት።
7. የእቅዱ መጽደቅ
እቅዱ በባለዕዳዋ/ው ተዘጋጅቶ፣ በተሳታፊ ባለገንዘቦች ተቀባይነት ያገኘ እንደሆነ ለፍርድ ቤቱ ቀርቦ ይጸድቃል። ፍርድ ቤቱ ካጸደቀ በኋላ ተፈጻሚ ይሆናል (ን.ሕ.ቁ 629)።
More Insights
View allReady to Discuss
Your Case?
Our advocates are ready to turn insight into action. Reach out for a confidential consultation.


